Job Requirements:
- የትምህርት ደረጃ :- ዕውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በማርኬቲንግ ወይም በቢዝነስ አድምንስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ ያላት
- ብዛት : – 1
- የሥራ ልምድ : – በደንበኞች አገልግሎት እና ቅሬታ አፈታት የሥራ መደብ በትንሹ ከ3 ዓመት በላይ የሰራ/ የሰራች
- ደመወዝ : – 9,000.00 ብር
ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ የሥራ ሃላፊነቶች :-
- ደንበኞችን በኩባንያው ሕግና መመሪያ መሰረት በአግባቡ የሚያስተናግድ፤
- ደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ በእቅድ በመመራት በየግዜው የሚከታተል፤
- የደንበኞችን ቅሬታ ተቀብሎ ፈጣን እና ተገቢውን ምላሽ በሰአቱ መስጠት የሚችል፤
- የሽያጭ እና የማርኬቲንግ መምሪያ ሥራዎች በስትራቴጂ በመንደፍ ማስቀጠል የሚችል፤
- የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ደንበኞች መምሪያው ዓመታዊ እቅድ እና በጀት አስተባብሮ መሥራት የሚችል፤
- ከማርኬቲንግ እና ሽያጭ ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችን ወስዶ ክፍሉን በዘመናዊ መልኩ ማደራጀት የሚችል፤
- የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት አድርጎ የተስተካከለ ዋጋ መስጠት የሚችል፤
- የደንበኞቻችንን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መረጃ በመሰብሰብ እና በመተንተን ለድርጅቱ የመከላከያ ስትራቴጂ ማዘጋጀት የሚችል፤ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ ሪፓርቶችን ማዘጋጀት የሚችል፤
ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች:-
የህክምና፣ የሀዘን፣ የደስታ፣ ዓመት ፍቃድ እና በሥራ ላይ ለሚገጥም ጉዳትም ሆነ ሞት ኢንሹራንስ፣ የሰርቪስ አገልግሎት፣ የቁርስ እና የምሳ አገልግሎት እንዲሁም ለቢሮ ሰራተኞች የልጆች ማቆያ አለው፤
How To Apply:
- የምዝገባ ቀናት፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት፤
- የምዝገባ ቦታ፡- መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ በስተጀርባ በኩል ፊት ለፊት በሚገኘው አስፋልት 600 ሜትር ላይ ላየን ሴኩሪቲ ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና መስሪያ ቤት፤
- አመልካቾች ለምዝገባ በሚቀርቡበት ወቅት የሥራ ልምድና የት/ማስረጃ ኦርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው
ለበለጠ መረጃ È 0922 46 40 43፣ 0118 69 60 92 እና [email protected]