Job Description:-
ኃላፊነት :-
- በዘርፉ ሥር የሚገኙ መምሪያዎችና ፋብሪካዎች ከኮርፖሬሽኑ እስትራቴጂያዊ ግቦች ጋር የተጣጣሙ ግቦች እንዲኖራቸው ማድረግ፣
- የተቀናጀ የዘርፉን እቅድና በጀት ማዘጋጀት በዘርፉም ስር የሚገኙ ፋብሪካዎች የኦፐሬሽናል ግቦች እንዲላኩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
- አዋጪነታቸው ተረጋግጦ ወደ ትግበራ የሚገቡ ፐሮጀክቶችን በመረከብ ኦፐሬሽናል ማድረግ ፣
- በዘርፉ ሥር የሚገኙ መምሪያዎችና ፋብሪካዎች የተቀናጀ አመታዊ እቅድ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
- የሥራ አስፈፃሚዎችንና ቡድን መሪዎችን ምልመላና መረጣ የኮርፖሬሽኑ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት ማከናወን፣
- የዘርፉን አፈፃፀም በየሳምንቱ ፣ በየወሩ ፣ በየእሩብ ዓመቱ፣ በየመንፈቅ ዓመትና በየዓመቱ ከሥራ አስፈፃሚዎች ጋር በመሆን እየገመገመ ሪፖርት ለዋና ሥራ አስፈፃሚ ማቅረብ፣
- የሥራ አስፈፃሚዎችን አፈፃፀም ውጤት ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት ይሞላል፣ በዋና ሥራ አስፈፃሚ በማጸደቅም ተግባራዊ ማድረግ፣
- ዘርፉን በመወከል ከውጪ አካላት ወይም ከተቋሙ ሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣
- የዘርፉ አፈፃፀም የሚሻሻልበትን ስልት በመቀየስ በሚመለከተው አካል ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ ማድረግ ፣
Job Requirements:
- ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ :- ፒ.ኤች.ዲ/ኤም.ኤስ ሲ/ኤም .ኤ/ቢ.ኤስ.ሲ/ቢኤ በማይኒንግ ፣ በማይ ሰርቬይ ኢንጂነሪንግ ፣ በጂኦሎጂ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም በተመሳሳይ በተጨማሪም ማኔጅመንት ዲቮሎፐመንት ስልጠና የወሰደ
- የሥራ ልምድ :- እንደቅደም ተከተላቸው በሙያው 8፣ 10፣ 12፣ ከዚህ ውስጥ 5 ዓመት በከፍተኛ ኃላፊነት የሠራ /የሠራች
- ደመወዝ :- 20,460.00
- የቅጥር ሁኔታ :- በቋሚነት
- የሥራ ቦታው :- አዲስ አበባ
- ብዛት :- አንድ ነው
How To Apply:
አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያላችሁን የሥራ ልምድና የትምህርት ማስረጃ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በሰው ሀብት ልማትና አመራር መምሪያ በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አድራሻ ፣ የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን 22 ማዛሪያ አውራሪስ ሆቴል በስተጀርባ ስልክ ቁጥር 0116-61-13-62 /0116-61-33-55
