Job Description
St. Gabriel General Hospital
St. Gabriel General Hospital PLC was established in September 1996 and is the first private hospital of its kind in Ethiopia. St. Gabriel General Hospital has paved the way and continues to provide access to healthcare to both the local and international community’s here in Addis. Over the past 22 years, the hospital has served over 400,000 patients in both Outpatient and Inpatient departments.
Our vision
We aim to deliver exceptional healthcare in a safe, compassionate, and caring environment that meets international standards. As a role model, St. Gabriel Hospital has and will continue to pave the way to accessible quality healthcare to both the local and international community.
የሥራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት
በሆስፒታሉ የሚሰጠው ህክምና አገልግሎት ደረጃውን ጠብቆ እንዲቀጥል በስራ ክፍሉ የሚገኙ ኃላፊ ነርሶችንና ነርሶችን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤ በአካል በመገኘት ነርሶች የሚሰጡትን አገልግሎት በየክፍሉ በመዘዋወር ምልከታ ያደርጋል፣ ክፍተቶች ሲኖሩም ወዲያውኑ ማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡
የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራት
- ሁሉም ኃላፊ ነርሶችና ነርሶች የስራ ሰአታቸውን አክብረው መገኘታቸውን ይቆጣጠራል፡፡ አርፍደው የሚመጡ ነርሶች ላይ ከምክርና ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተገቢውን የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡በተደጋጋሚ ያሚያረፍዱ ኃላፊ ነርሶች ሲኖሩም ሪፖርት ያደርጋል፡፡
- ያለፈቃድ ከስራ የሚቀሩ ኃላፊ ነርሶች ወይም ነርሶች ሲያጋጥሙ ከግማሽ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ለአስተዳደር ሪፖርት ያደርጋል፡፡
- በየክፍሉ የሚገኙ ነርሶች የውሎና አዳር ርክክብ በአግባቡ መከናወኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤ ክፍተቶች ሲኖሩም የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
- ሁሉም በስሩ የሚገኙት ሠራተኞች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል
- ከህመምተኞች ቁጥር ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ ነርሶች መኖራቸውን ወይም መመደባቸውን ይከታተላል ክፍተቶች ካሉም የማሸጋሸግ ስራ ይሰራል፤
- ተኝተው የሚታከሙ ህመምተኞች ተገቢውን ምግብና መድሃኒት በተገቢው ሰዓት እየቀረበላቸው መሆኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- የመኝታ ክፍሎችና ህክምና መስጫ አካባቢዎች ንፅህናቸው የተጠበቀ መሆኑንና አስፈላጊው መሳሪያ የተሟላላቸው መሆኑን ይከታተላል፣ ካልተሟላና ንፅህናቸው ካልጠተበቀ እንዲስተካከል ያደርጋል፤
- ሀመምተኞች ሰብኣዊ ክብራቸው ተጠብቆ፣ በትህትናና በእንክብካቤ ህክምና የተሰጣቸው መሆኑን ያረጋግጣል፤
- ከህመምተኞችና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የቀረበ ግንኙነት በመፍጠርና ችግሮቻቸውን በማድመጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
- ነርሶች በድንገተኛ አደጋዎች ወቅትና ከአቅም በላይ ታካሚ በሚኖርበት ወቅት በምን መልኩ ስራቸውን ተረጋግተው መስራት እንዳለባቸው የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጁነት ስልጠናዎችን ይሰጣል ወይም እንዲያገኙ ያደርጋል፤
- በሆስፒታሉና ታካሚዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚገኙ መሳሪያዎችና ክፍሎች በማንኛውም መንገድ እንዳይበከሉ ተገቢውን ጥንቃቄ መደረጉን ዝወትር ይቆጣጠራል፤
- አዲስ ለሚቀጠሩ ነርሶች ተገቢውን ስልጠና ይሰጣል.፣ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- የሆስፒታሉን ንብረቶች በእንክብካቤ መያዛቸውን የመቆጣጠር፣ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለበት ተገንዝቦ ይህንኑ በስሩ ለሚገኙት ሠራተኞች ያሳውቃል፡፡ በማንኛውም ጊዜ የንብረት ርክክብ በትክክል መፈፀሙን ይቆጣጠራል፡፡
- የኃላፊ ነርሶችን የስራ አፈፃፀም ለመገምገም የሚያስችሉ መረጃዎችን ይይዛል፤ ድርጅቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት የሥራ አፈፃፀማቸውን ከበላይ ኃላፊ ጋር በመሆን ይሞላል፣ ለአስተዳደር በወቅቱ ያስተላልፋል፡፡
- ተረኛ ኃላፊ ነርስ በሥራ ላይ መገኘት ባይችል በወቅቱ ፕሮግራሙን አስተካክሎ ሠራተኛ ይመድባል፤ሠራተኛ መመደብ በማይቻልበት ጊዜ እራሱ የቀረውን ሠራተኛ ቦታ ሸፍኖ ይሰራል፡፡
- ከአስተዳደር የሚላኩትን ማስታወቂያዎችም ሆነ ሌላ ማስታወሻ ለሠራተኞች በግልፅ ቦታ እንዲለጠፍና መልዕክቱ እንዲደርስ ያደርጋል የተባለውም በስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፡፡
- ከበላይ ኃላፊው ለሠራተኞች እንዲተላለፍ የተነገረውን መልዕክት ወዲያውኑ በስሩ የሚገኙትን ኃላፊ ነርሶች ሰብስቦ ማስረዳትና ተግባራዊነቱን መከታተል፡፡
- በየጊዜው በስሩ ከተመደቡት ሠራተኞች ጋር በመወያየት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ወቅቱን የጠበቀ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፣ በቡድኑ የመማማር እና የመረዳዳት ባህል እንዲኖር የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
- አዳዲስ ግኝቶችና የቴክኖሎጂ ለውጦች ሲኖሩ ራሱንና በስሩ የሚገኙትን ሠራተኞች እንዲያውቁ ያደርጋል፡፡
- ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ተጨማሪ ክህሎቶች
- ከፍተኛ የመግባባት/የማዳመጥና የማስረዳትና ምሳሌ በመሆን የመምራት ችሎታ፣
መሰረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀት
Job Requirements
Requirements
- BSc degree in Nursing
- A minimum of 8 years experience from which at least 3 years as a matron or D/matron
- Renewed health professional License Certificate is mandatory.
- Basic Computer skill
Required Number: 01 (one)
How to Apply
All interested and fulfilled applicants should send a Curriculum Vitae only by email to stgabrielghospitalhr@gmail.com or non returnable copies of all credentials to the Administration office no 112
Address: Addis Ababa, Bole sub city, Woreda 04, 22 Mazoria on the way to Bole Medhaniyalem Church in front of Awraris Hotel. For additional Information Tel No. 8819.
Note: Please note that only short-listed candidates will be contacted