Job Expired

company-logo

Corporate Operation Sector Manager

Chemical Industry Corporation

job-description-icon

Engineering

Chemical Engineering

Addis Ababa

Position

2021-06-11

to

2021-06-17

Required Skills
Required skills have not yet been specified for this position this job
Fields of study
No fields of study

Full Time

Share

Job Description

  • በሥራ መደቡ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የኮርፖሬት ኦፕሬሽን መምሪያ ሥራ አስፈፃሚ ተጠሪነቱ ለኮርፖሬት ፕሮጀክትና ኦፕሬሽ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራትን ያከናውናል፡፡

  • የመምሪያውን ሥራ ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፣
  • የኮርፖሬሽኑ ፋብሪካዎች የምርትና ቴክኒክ ሥራዎች በታቀደው መሰረት እየተከናወኑ ስለመሆኑ የቅርብ ክትትል ያደርጋል፣ያልተቋረጠ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣ለፋብሪካዎቹ ምርቶች ገበያ የማጥናትና የማፈላለግ ዕገዛ ያደርጋል፡፡
  • በተጠሪ ፋብሪካዎች የሚገኙ የማምረቻና ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎች ያለ ችግር መሥራታቸውንና ተገቢው እንክብካቤና የመከላከል ጥገና እየተደረገላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፣ ብልሽት ሲያጋጥም በወቅቱ የጥገና አገልግሎት ማግኘታቸውንም ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
  • በተጠሪ ፋብሪካዎች መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎችና ሌሎች የመገልገያ መሣሪያዎች በበቂ ክምችት እንዲኖር እገዛ ያደርጋል፣
  • የፈጠራንና አስመስሎ/ሞዲፊኬሽን/ የመሥራት ተግባሮች የሚዳብሩበትንና የሚስፋፉበትን መንገድ ያመቻቻል፣
  • የማምረቻ መሣሪያዎች የማምረት ብቃት የሚሻሻልበትን ዘዴ ይቀይሳል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • የኮርፖሬሽኑን የግዢና ሽያጭ ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ያዘጋጃል፣ ሲፀድቁም በትክክል ተፈጻሚ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
  • ማናቸውም ግዢዎችና ሽያጮች በመንግስት መመሪያና ደንብ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ የግዢ እና ሽያጭ መመሪያ መሰረት እንዲፈጸሙ ይከታተላል፣
  • በኮርፖሬሽኑየምርት ዕቅድ መሠረት ለምርት ሥራ የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎች፣ መለዋወጫዎች፣ እንዲሁም አላቂና ቋሚ ንብረቶች በዓይነትና በመጠን በወቅቱ ተሟልተው እንዲገኙ ለማድረግ የሚያስችል የግዥ ዕቅድ ከሚመለከታቸው ፋብሪንዎች ጋር ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
  • ከውጭ ለሚገዙ ዕቃዎች የኢንሹራንስ፣ የጉምሩክና የወደብ ርክክብ ፎርማሊቲዎች በአግባቡ መሟላታቸውንና ዕቃዎቹ በትዕዛዝ መሠረት ተሟልተው የመጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ በዓይነትም ሆነ በመጠን ልዩነት ሲያጋጥም ወዲያውኑ ለኢንሹራንስ በማሳወቅ ዕቃው እንዲሟላ ወይም ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን ድጋፍ ይሰጣል፡፡
  • የሥራ መደቡ የሚፈልገው ዕውቀትና ክህሎት
  • በአምራች (Manufacturing) ዘርፍ የኦፕሬሽን ስራዎች ላይ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያለው/ያላት፣
  • የኦፕሬሽን ሥራዎችን በመምራትና ውጤታማ በማድረግ የተረጋገጠ ልምድና ብቃት ያለው/ያላት፣
  • የተግባቦትና የማስተባበር ክህሎት ያለው/ያላት፣
  • የሥራ ውጥረትን ተቋቁሞ ለረጅም ሰዓታት የመስራት ብቃት ያለው/ያላት፣
  • የግዥና የገበያ ጥናቶችን የመተንተን እንዲሁም ትግበራውን የማሳለጥ ልምድና ክህሎት ያለው/ያላት፣
  • የግዥና የሽያጭ ፖሊሲዎችን፣መመሪያዎችንና ደንቦችን የማዘጋጀትና በበላይነት የማስተባበርና የማስተግበር ዕውቀትና ክህሎት ያለው/ያላት፣

Job Requirement

  • ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡- ማስተርስ/ቢኤ.ስሲ
  • ተፈላጊ የትምህርት ዓይነት፡-ኬሚካል፣መካኒካል፣በማይኒንግ፣ኢንዱስትሪያል፣ኤሌክትሪካልኢንጂነሪንግ ወይም ኬሚስትሪ፣በኢኮኖሚክስ፣ በማኔጅመንት/ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን

የሥራ ልምድ፡-

  • በመጀመሪያ ዲግሪ ለአጠናቀቀ/ች 10/12 ዓመት፣
  • በሁለተኛ ዲግሪ ላጠናቀቀ/ች 8/10 ዓመት
  • ደረጃ፡- XIV
  • ጥቅማ ጥቅም፡-ጥቅማ ጥቅም፡- በኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት (የኃላፊነትአበል፣ህክምና፣የመድህን ዋስትና፣መኪና ከነዳጅ ጋር ወዘተ) ይሰጣል፡፡፡

ደመወዝ፡ 25,958 ብር /ሃያ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት ብር/

How to Apply

  • ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት፣የሥራ ልምድና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎቻችሁን ዋናውን ከማይመለስ ኮፒ ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ እንድታመለክቱ እናስታውቃለን፡፡
  • አድራሻ፡- ቦሌ ከፍሬንድሺፕ ሱፐር ማርኬት ወይም ዲ.ኤች ገዳ ህንፃ ወደ ውስጥ 2ዐዐ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ በኮርፖሬት የሰው ሀብትና ፋሲሲቲ ሥራ አመራር መምሪያ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ስልክ 0116183937/ 0116624326 ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን


Related Jobs

5 days left

Kadisco Paint and Adhesive Industry S.C

Production - Intern

Internship

time-icon

Internship

0 - 1 yrs

1 Position


Bachelor’s Degree in Chemistry, Industrial Chemistry, Applied Chemistry, Chemical Engineering or in a related field of study Duties and Responsibilities: - Assist the Production In-Charge with routine daily tasks. - Support data collection, documentation, and record-keeping activities. - Provide hands-on assistance during critical operations to help reduce bottlenecks, especially during peak production periods.

Addis Ababa

14 days left

Abays Trading PLC

Quality Control and Quality Assurance Officer

Quality Control Expert

time-icon

Full Time

2 yrs

3 Positions


BSc Degree or Diploma in Food Engineering, Chemical Engineering, Food Science or in a related field of study with relevant work experience Duties and Responsibilities: - Ensure that production standards are met and maintained for a given product before it leaves the place  - Perform inspections on random samples from a production line; identify defects in the manufacturing process and correcting them.  - Organize inspections according to internal and legal standards. Ensure that a quality product is delivered for consumers -  Analyze testing results and the frequency and severity of product defects and quality lapses.

Sululta