የስራው መደብ ዝርዝር
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ቀጥሎ በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፤ለመወዳደር የሚፈልጉ አመልካቾች በተጠቀሰው ቦታና ቀን ማመልከት ይችላሉ፡፡
ተፈላጊ ችሎታ: በአፈር ሣይንስ ወይም በአፈር ማይክሮባዮሎጂ የሙያ መስክ ኤም.ኤስ.ሲዲግሪ ያለው/ያላት፤ የሚቀርብ የሥራ ልምድ በምርምር ወይም በሙያው በማስተማር መሆን አለበት፣
የሥራ ቦታ: አሶሳ፣ፓዌ፣ወረር እና ሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከላት
ብዛት: 4(አራት)
Applicant Instruction | የአመልካቾች መመርያ
ማሳሰቢያ ለተመዝጋቢዎች፤
- የምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው፣
- የምዝገባ ቦታ በኢንስቲትዩቱ ዋናው መሥሪያ ቤት በሰው ሀብት ሥራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ነው፣
- የግብርና ተመራማሪዎች ደመወዝ በግብርና ተመራማሪዎች የደመወዝ ስኬል መሰረት ነው፣
- በሁሉም የግብርና ተመራማሪ የሥራ መደቦች ላይ የሚወዳደሩ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ ነጥብ (CGPA) ውጤቱ ለሴት 00 እና በላይ ለወንድ 3.25 እና በላይ መሆን አለበት፣
- አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው፤ለሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ማመልከቻ መጻፍ አለባቸው፤የተሟላካሪኩለም ቪቴ (CV) የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፤ በቂ የስልክ ወይም አማራጭ አድራሻ የስልክ ቁጥሮች በማመልከቻው ላይ መግለጽ ይኖርባቸዋል፣
- ለመወዳደር የሚፈልጉ አመልካቾች በግንባር እየቀረቡ ወይም በወኪል ወይም በፖስታ ልከው መመዝገብ ይችላሉ፣
- የምዝገባ አድራሻ፡-መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በአምቼ ኩባንያ በኩል ወይም በጂኦሎጂካል ሰርቬይ በኩል ገባ ብሎ ነው፣
- ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጽ እና www. ethiojobs.net ፣ የስልክ ቁጥር 0116-45-44-41 እንዲሁም የፖ.ሣ.ቁ. 2003 (አዲስ አበባ) መጠቀም ይቻላል፣
- ሴት አመልካቾች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡
- የምዝገባው ጊዜ ከ ሐምሌ07 2013 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 21 2013 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት