Super SGS Trading
Education
Education Management
Addis Ababa
3 years - 15 years
10 Positions
2025-05-12
to
2025-06-07
demonstrate when teaching
adapt teaching to target group
Accounting
Linguistics and languages
Graphic Design
Full Time
Share
Job Description
ድርጅታችን SuperBoostUp/Beleqet E-learning የምንሰጥ ሲሆን ለዚሁ የሚረዳ LMS (Learning Management System) ፕሮፌሽናል የሆነ ፕላትፎርም አዘጋጅተናል፡፡ በዚህም በመስኩ የመሪነት ቦታ ያለን የትምህርታዊ ሂደት ፕላትፎርም ባለቤቶች ነን።
ማንኛው ሰልጣኝ(ተማሪ) ያለበት ትምህርት ደረጃ፣ ቦታ ሳይገድበው በእራሱ ላይ ክህሎት በመጨመር የተሻለ እውቀት፣ የገቢ ምንጭ ማግኘት የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር ሲሆን ለዚህ ራዕይ/ተልኮ በቂ የሆን የማሰልጠን ልምድ ያላቸው ፕሮፌሽናሎችን ማሰራት እንፈልጋለን፡፡
ብዛት፡ 10
አስተማሪዎች ከሚያገኙት ጥቅሞች መካከል፡-
ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው የ'ፕሮዳክሽን መገልገያዎች፣ እስቱዲዮ፣ እና ባለሙያዎች በመጠቀም የማስተማር ተግባርዎንና ሂደቱን በሚያሳልጡ መንገዶች የተዘጋጁትን የኛን መገልገያዎች ተጠቅመዉ በአመርቂ ሁኔታ ክህሎቶን ማውጣት ይችላሉ።
ስኬትን ለማረጋገጥ የሚተጉ በየዘርፉ ፕሮፌሽናል የሆኑ እና ከፍተኛ ልምድ፣ እውቅና ያለቸው እስከ ፒ.ኤች.ዲ(Dr) ድረስ ያሉ አሰልጣኞች የተሰባሰቡበት በመሆኑ የእርሶን የማስተማር አቅምና ልምድ የሚጨምሩበት ነው፡፡
ቀጣይነት ያለው(Passive Income) ገቢ የማግኘት ዕድል ይፈጥራሉ፡፡
በቦታና ርቀት ሳይገደቡ ከአገር ውስጥ አልፎ በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙያዉን ለሚፈልጉ ማደረስ የሚችሉበት ሁኔታዎችን መፍጠር፡፡
በመሆኑም በቂ የሆነ ግብዓት(ኮርስ) እና ልምድ ያለው አመልካች ከታች በቀረቡት ሃሳቦች አብሮ ለመስራት አማራጮች ቀርበዋል፡፡
የኦንላይን(online) ስልጠናዎችን ለመስጠት፣ ለዚህም ይረዳን ዘንድ የተለያዩ ስልጠና መስጠት የሚችሉ አሰልጣኞችን አወዳድረን ማሰራት እንፈልጋለን፡፡
ከዚህ በፊት የስልጠና ማንዋል እና በየትኛውም ፕላትፎም ላይ በቪዲዮ ፎርማት የተዘጋጀ ያለው ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
የስልጠና ማንዋል ያለው ግን አሁንም ላይ በእራሱ ቦታ ፕሮዳክሽን(ቀረፃና ኢዲቲንግ) መስራት የሚችል፡፡
ሌላው እኛው ጋር ባዘጋጀነው ፕሮዳክሽን (ቀረፃና ኢዲትንግ) ቦታ ላይ የራሱን ማንዋል (ኮርሶችን) ይዞ በመምጣት ለኦንላይን ስልጠና የሚሆን ቪዲዮ መስራት የሚችል ሲሆን፡-
በግራፊክስ ዲዛይን፣ Youtube፣ አካውንቲንግ እና ፒችትሪ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ቋንቋ (ኢንግሊዘኛ፣ ቻይንኛ...)፣ ትሬድ (ፎራኤክስ ትሬዲንግ፣ ስቶክ ትሬዲንግ፣ ክሪፕቶ ከረንሲ)፣ ሜካፕ፣ AI መስኮች፣ ቢያንስ የሶስት አመት የማስተማርና የማሰልጠን ልምድ
በቅርብ ክትትል አማካይኝት የተመሰከረለትና(የተረጋገጠ) ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የትምርት ኮንቴንት የማዘጋጀትና የማቅረብ ልምድና ክህሎት ያለው
ጠንካራ የሆነ የእርስ በእርስና የማህበራዊ ግንኙነት ክህሎት ያለው
የማስተማር ዘዴዎቹን የተለያዩ ከሆኑ የተማሪዎች ፍላጎቶች ጋር ማጣጣም የሚችል
ኦንላይን ላይ የማስተማር እውቀትና ልምድ ያለው ቅድሚያ ይሰጠዋል።
ከኛ በኩል አጥብቀን የምንሻቸው ገጽታዎች
ልዩ ትምርታዊ ልምዶችን ስለማቅረብና ማካፈል ተግባር፣ ጠንካራና የሚታመን ፍላጎት ያላቸውን ምምህራን የበለጠ ተመራጭነት የሚኖራቸው ሲሆን፤ በተማሩት ትምርት(መስክ) ዙሪያ ጠንካራ የእውቀት መሠረት ያላቸውና የተማሪዎችን የተሳትፎ ደረጃ ከፍ ማድረግ የሚችሉ።
ከፍተኛ ደረጃ ያለው ፕሮፌሽናል(ባለ ልዩ ሙያ) ከሆኑና በተማሪዎች ላይ አውንታዊ አንድምታ በመፍጠር ተጨማሪ( Passive Income) ገቢ ለማግኘት የሚሹ ከሆኑ፤ የስራ ልምድዎትን እና የትምርት ማሰስረጃዎን በማያያዝ በቴሌግራም ይህን ሊንክ በመጠቀም ሊልኩልን ይችላሉ።
የወደፊቱን የትምርት እድገትና ሂደት ለመቅረጽ በሚደረገው ርብርብ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ እኛን ይቀላቀሉ።
ክህሎት ያላቸው መምህራን ሁሉ ከኛ ጋር እንዲቀላቀሉ በጉጉት እንጠብቃለን።
ማሳሰቢያ፡ አብዛኞውቹ ኮርሶች ፕሮፌሽናል በሆኑ ኢንስትራክተሮች የማስተማር ሂደቱ ተጠናቆ ትምህርት ለመስጠት ሁሉን ዝግጅት የጨረሰን ሲሆን፤ ከታች በተዘረዘሩት ዘርፍ ልምድ እና የማሰልጠን ዝግጁነት ያላችሁ ቅድሚያ የምንሰጥ ይሆናል(ነው)፡፡
Fields Of Study
Accounting
Linguistics and languages
Graphic Design
Skills Required
demonstrate when teaching
adapt teaching to target group