Job Expired

company-logo

Production & Technical Department Head

Minaye PLC

job-description-icon

Engineering

Mechanical Engineering

Addis Ababa

6 years - 7 years

1 Position

2024-06-25

to

2024-06-28

Required Skills
Required skills have not yet been specified for this position this job
Fields of study

General Mechanic/Industrial Technology

Mechanical Engineering

Industrial and Manufacturing Engineering

Full Time

Share

Job Description

የመምሪያውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት፣ መቆጣጠር፣ አስፈላጊ የሆኑ የሥራ መሣሪያዎችና የምርት መገለገያ መሣሪያዎች በትክክል ተጠግነው ፋብሪካው ያለማቋረጥ ማምረቱን መከታተልና መቆጣጠር፣ የምርት ጥራት ተፈላጊውን ደረጃ የያዘ መሆኑን በማረጋገጥና በተፈለገው መጠንና አይነት እንዲመረት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ በሥሩ የሚገኙ የሥራ ዘርፎች በተቀናጀ መልኩ የምርት ማምረት ተግባራቸውን ማከናወናቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፣ ጥሬ ዕቃዎችና መለዋወጫዎች በወቅቱና በተፈለገው ጥራት መታዘዛቸውንና መቅረባቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፣ የፋብራካው የምርት በጥራት በአይነትና በመጠን የሚያድግበትን ጥናት በማካሄድ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፣ የድርጅቱን የማምረቻና ተጓዳኝ መሣሪያዎችን፣ የማምረቻና የቢሮ ሕንጻዎች፣ የቧንቧና ፍሳሽ መስመሮችን መንከባከብ፣ መጠገን፣ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በሚፈለገው ዓይነትና መጠን በክምችት እንዲኖር ማድረግ፣ በፋብሪካው የምርት ሂደት መሠረት ሠራተኞች፣ ጥሬ ዕቃዎችና የማምረቻ መሣሪያዎች ቅልጥፍናና ቁጠባ በተሟላበት ዘዴ ተቀነባብሮ ከፍተኛ ምርት የሚገኝበትን አሠራር ተግባር ላይ ማዋል፣ ስለምርትና ቴክኒክ የሥራ እንቅስቃሴ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ማቅረብ።

ዝርዝር ተግባራት

  • የመምሪያውን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ በሥሩ የሚገኙትን ኃላፊዎችና ሠራተኞችን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ አስፈላጊ የሆኑ የሥራ መመሪያዎችንም ያስተላልፋል፣ በተግባር መተርጎማቸውንም ይቆጣጠራል፤

  • በፋብሪካው የምርት ዕቅድ መሠረት ጥራት ያለው ምርት በተፈለገው መጠን፣ ጥራትና አይነት መመረቱን ይከታተላል፣ የማምረቻ መሣሪያዎችን ጥገናና እንክብካቤ በሥሩ ባሉ ሁሉም የማምረቻ ቦታዎች በተቀነባበረና በተሟላ ሁኔታ መከናወኑን ይቆጣጠራል፤

  • ምርት የምማረት ሥራ ከመጀመሩ አስቀድሞ የማምረቻ መሣሪያዎች የተስተካከሉ መሆናቸውንና ለምርት ሥራ የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎችና ኬሚካሎች፣ ቁሳቁሶች በተመጣጠነ የክምችት መጠን እንዲገኙ የሚመለከታቸውን የሥራ ዘርፎች ያሳስባል፣ ከምርቱ ዕቅድ ጋር የተነጻጸረ ክምችት መኖሩንም ይከታተላል፣ያረጋግጣል፤

  • የማምረቻ መሣሪያዎች ጥገና በየዓይነታቸው በመለየት ምን ዓይነት ጥገና እንደሚያስፈልጋቸውና ጥገናው በማን መቼና የት እንደሚካሄድ፣ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ የሚገልጽ ዓመታዊ የጥገናና የመሣሪያዎች እንክብካቤ ፕሮግራም እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤

  • ጥራት ያለው ምርት በተፈለገው አይነት መጠንና መረጃ እንዲመረት ያደርጋል፣ የምርት ብልሽት ወይም ጥራት ጉድለት ሲያጋጥም ከሚመለከታቸው ባለ ሙያዎች ጋር በመሆንና በማጥናት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ጥራቱ እንዲጠበቅ ያደርጋል፤

  • በዓመቱ የምርት ዕቅድ መሠረት የሚመረተውን የምርት መጠን ከተጠቃሚ ደንበኞች ፍላጎት ጋር ለማዛመድ የዕለት፣ የሳምንትና የወር የምርት ፕሮግራም ከሚመለከታቸው የሥራ ዘርፎች ጋ በመተባበር ያወጣል፣ በሥራ ላይ መዋሉንም በቅርብ ይቆጣጠራል፤

  • የምርት ውጤቶችና ለምርት ተግባር የሚውሉ ልዩ ልዩ ጥሬ ዕቃዎችና መሣሪያዎችም እንዳይበላሹና ኢኮኖሚያዊ ባልሆነ መንገድ ሥራ ላይ እንዳይውሉ ይቆጣጠራል፣ ጥንቃቄም እንዲደረግ አስፈላጊውን የሥራ መመሪያ ይሰጣል፤

  • ለየሥራ ዘርፎች የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ከስራዎቹ ባህሪ ጋር በተጣጣመ መልኩ መሟላቱን ያረጋግጣል፣ በፋብሪካው ውስጥ፣ የሚገኙ የምርትና ቴክኒክ ባለሙያዎች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ በሚመለከታቸው የሥራ ዘርፎች ጋር በመመካከርና በማጥናት ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

  • የምርት ስታትስቲካዊ መረጃዎች በየወቅቱ እንዲዘጋጁና የሚመረተው ምርት ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ከጥራት ቁጥጥር፣ ከንግድና ፋይናንስ የሥራ ዘርፎች የሚደርሱትን የማሻሻያ ሃሳቦችና አስተያየቶች በማሰባሰብና በማጥናት በሥራ እንዲተረጉም ያደርጋል፤

  • በመሣሪያዎች፣ በመለዋወጫዎችና በተሽከርካሪዎች ግዥ ወይም የአገልግሎት ኪራይ ወቅት ቴክኒካዊ ምክርና አስተያየት ይሰጣል፣ በልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መለዋወጫዎች ግዥ ላይ የአያያዝና የአጠቃቀም መግለጫዎችና አስረጂ ሠነዶች ተሟልተው መገኘታቸውን ያረጋግጣል፣ በተከላ፣ በመለወጥና በጥገና ወቅትም ሥራው በተገቢው ጥራት መከናወኑን ይቆጣጠራል፤

  • የማምረቻ መሣሪያዎች የጥገናና የእደሣ ፕሮግራም በታቀደለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማከናወን የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ አገልግሎት ሰጪ የሥራ ዘርፎችን ያሰባስባል፣ በሥሩ የሚገኙትንም ባለሙያዎች በማስተባበርና በማሰባሰብ የጥገናና የእድሳት ፕሮግራም በተግባር መተርጎሙን ያረጋግጣል፤

  • ለሥራ ዘርፉ የተመደቡት ሠራተኞች ዕቃዎችና መሣሪያዎች ከማናቸውም አደጋ እንዲጠበቁ ጥንቃቄ መደረጉን ፣ ማናቸውንም የምርቱን ሂደት የሚያሰናክል ሁኔታ ቢደርስ ወዲያውኑ እርምጃ መወሰዱን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

  • መሣሪያዎችን ለሚያንቀሳቅሱ ሠራተኞችም ተገቢውን የሥራ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ኢንዱስትሪያል ሴፍቲ ሕጎችን እንዲያከብሩ መመሪያ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤

  • በተለያዩ ምክንያቶች በምርት ዕቅድና በተገኘው የምርት ውጤት መካከል ልዩነት ሲያጋጥም የልዩነቱን ምክንያት በማጥናት የሚስተካከልበትን መንገድ ያጠናል፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑ የአሠራር ዘዴዎች እንዲሰፍኑና በአነስተኛ ወጪ ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለማምረትና ለማሻሻል አዳዲስ የምርት ዓይነቶችንም ለማምረት የሚያስችሉ ጥናቶችና ምርምሮች እንዲደረጉ ጥረት ያደርጋል፤

  • መምሪያው ከስቶር የሚረከባቸውን ጥሬ ዕቃዎችና ኬሚካሎች ለተለያዩ የምርት ውጤቶች በተገቢው መጠን በአገልግሎት ላይ እንዲውሉና የተመረውም የምርት ዝርዝር እየተዘጋጀ ለፋይናንስ የሥራ ዘርፍ መተላለፉን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

  • የመምሪያው በጀት ዕቅድና የሥራ ፕሮግራም እንዲሁም ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች የተከናወኑ ተግባራትን እና ያጋጠሙ ችግሮች ከመፍትሄ ሃሳብ ጋር እያዘጋጀ ያቀርባል፤

  • እንዳስፈላጊነቱ ከዋና ሥራ አስኪያጅ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፡፡

የስራ መስፈርቶች

  • ዲግሪ በጠቅላላ መካኒክ፣ መካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ ኢንደስትሪያል እና ማኑፋክቸሪንግ ኢንጂነሪንግ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች ከዚህ ውስጥ 3 ዓመት በማኔጅመንት የሰራ/ች

የስራ ልምድ

  • 6-7 ዓመት በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ላይ የስራ ልምድ ያለው/ላት

የማመልከቻ መመርያ

  • አመልካቾች የትምህርት፣ የሥራ ልምድ ደብዳቤ የማይመለስ ኮፒ ይዛችሁ በድርጅቱ ኢ-ሜይል hrminaye@gmail.com ወይም ቃሊቲ ገብርኤል ኢንዱስተሪያል መንደር አካባቢ ዴሉክስ ፈርኒቸር ፋብሪካ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። ለበለጠ መረጃ ስልክ 0114717381

Fields Of Study

General Mechanic/Industrial Technology

Mechanical Engineering

Industrial and Manufacturing Engineering

Related Jobs

6 days left

Bio Safe Trading PLC

Engineering Technician

Technician

time-icon

Full Time

0 yrs

1 Position


Bachelor's Degree in Biomedical Engineering, Chemical Engineering, Computer Engineering, Mechanical Engineering or in a related field of study Duties & Responsibilities: - Prepare and submit project documents - Design, control, and implement engineering laboratory machines and products - Install, configure and test engineering laboratory machines - Training and commissioning of projects - Develop manufacturing processes according to global engineering codes and standards

Addis Ababa

about 18 hours left

GCL Energy Investments Limited

LNG gasification operator

Mechanical Engineer

time-icon

Full Time

1 - 3 yrs

1 Position


Bachelor's Degree in Mechanical Engineering, or in a related field of study, with relevant work experience Duties & Responsibilities: - LNG gasification and gas supply operation under the lead of the line manager

Tulefa

about 18 hours left

GCL Energy Investments Limited

Maintenance and Repair Technician

Maintenance Technician

time-icon

Full Time

1 - 3 yrs

1 Position


BSc Degree in Mechanical Engineering or in a related field of study with relevant work experience

Addis Ababa

about 18 hours left

GCL Energy Investments Limited

LNG Refilling Operator

Mechanical Engineer

time-icon

Full Time

1 - 3 yrs

1 Position


Bachelor's Degree in Mechanical Engineering, or in a related field of study, with relevant work experience Duties & Responsibilities: - LNG filling operation under the lead of the line manager

Jijiga

about 18 hours left

Aforo Trading PLC

Mechanical Engineer

Mechanical Engineer

time-icon

Full Time

2 yrs

1 Position


Bachelor's Degree in Mechanical Engineering, Electromechanical Engineering, or in a related field of study with relevant work experience Duties & Responsibilities: - Develop and implement preventive and predictive maintenance plans to minimize downtime and ensure operational efficiency. - Supervise and coordinate maintenance activities, including the repair and servicing of equipment and machinery. - Lead, train, and evaluate the maintenance team to ensure high levels of performance and adherence to safety standards

Semera

about 18 hours left

Wat International plc

Project Engineer

Project Engineer

time-icon

Full Time

5 yrs

1 Position


Bachelor's Degree in Electrical, Mechanical Engineering or in a related field of study with relevant work experience, out of which 2/3 years of experience in water supply and power generation projects

Addis Ababa