Job Expired
Minaye PLC
Business
Human Resource Management
Addis Ababa
3 years - 4 years
1 Position
2024-06-26
to
2024-06-28
Public Administration
TVET
Management
Full Time
Share
Job Description
ክፍሉን ሥራ ማቀድና ማደራጀት፣ ማስተባበር፣ መምራትና መቆጣጠር፣ የድርጅቱን የሰው ኃይል ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር እንዲሁም ስንብት ፎርማሊቲን ማከናወን፣ በሠራተኞች ዘንድ የሥራ ዲሲፕሊን እንዲከበር ማድረግ፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የስልክ፣ የትራንስፖርትና የጥበቃ፣ የጽዳትና የመላላክ የፎቶ ኮፒ አገልግሎት የተሟሉ መሆናቸውን መከታተልና መቆጣጠር፣ የድርጅቱን መኪናዎች ለስራ ማሰማራትናመቆጣጠር፣ የመኪኖቹን ደህንነት ማረጋገጥ፣ልዩ ልዩ የሥራ ልብሶች በወቅቱ ለሠራተኛው መድረሳቸውን ማረጋገጥ የጠቅላላ አገልግሎት ሥራዎች የሚቀላጠፉበትንና የሚሻሻሉበትን መንገድ በማጥናት ማቅረብና ሲፈቀድ ሥራ ላይ ማዋል።
የስራ ቦታ :-ቃሊቲ
የዋና ክፍሉን ሥራ ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ በሥሩ ያሉትን ሠራተኞች ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
በድርጅቱ የአስተዳደር ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት የድርጅቱን የሰው ሀይል ያስተዳድራል፣ ቀልጣፋ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤
በተለያዩ ምክንያት ድርጅቱን በሚለቁ ሠራተኞች ምትክ ተገቢው የሰው ኃይል እንዲተካ ለሚመለከታቸው የዘርፍ ሃላፊዎች ያሳውቃል፣ለቅጥሩም ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፤
ለድርጅቱ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የውኃ፣ የመብራት፣ የስልክ፣ የነዳጅ፣ የትራንሰፖርት፣ እንዲሁም ኢንሹራንስ፣ ለመዝናኛ ክበብ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች መሟላታቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ያልተሟሉ መገልገያዎችና ዕቃዎች ካሉ እንዲሟሉ ዝርዝር ሪፖርት ለቅርብ አለቃው ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
የጠቅላላ አገልግሎት ሥራ በተሻለ ቅልጥፍናና ጥራት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ጥናት በማድረግ ለሃላፊው አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፤ ለክፍሉ የሚያስፈልገውን በጀት በማዘጋጀት ያስፈቅዳል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል ያረጋግጣል፤
የድርጅቱ የግቢ ጥበቃ አስተማማኝ መሆኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
ለድርጅቱ ሠራተኞች የሚያስፈልጉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ መሣሪያዎችና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች በወቅቱ መሟላታቸውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፤
በድርጅቱ ደንብና መመሪያ መሠረት ለሠራተኞች መስጠት የሚገባው የሥራ ላይ የአደጋ መከላከያ የሥራ ልብስና የመሳሰሉት በወቅቱ እንዲደርሳቸው ያደርጋል፡፡
በኢንሹራንስ ፖሊሲ መሠረት የድርጅቱ ንብረትና የድርጅቱ ሠራተኞች የመድን ዋስትና ማግኘታቸውን ይከታተላል፤ በየዘመኑ መታደሱን ያረጋግጣል፤
በንብረት ወይም በሰው ላይ አደጋ በደረሰ ጊዜ በተገቢው የመድን ዋስትና መሠረት የካሳ ጥያቄ /claim/ በማድረግ ተከታትሎ ያስፈጽማል፤
የተሽከርካሪዎች የሕይወት ታሪክ፣ የነዳጅና የቅባት ፍጆታ የጥገና ወጪን በተመለከተ አስፈላጊ መረጃዎች በሙሉ መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
ማንኛውም የድርጅቱ ንብረት ተገቢ ጥበቃና ጽዳት የተሟላ መሆኑን፣ የቢሮ መሣሪያዎች፣ ቋሚ ንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎችና ሕንፃዎች አስፈላጊው ጥገናና ዕድሳት በሚያስፈልጋቸውና ከቅርብ አለቃው ሲፈቀድ በሚተላለፍለት መመሪያ መሠረት ጥገናዎቹ በወቅቱ እንዲከናወኑ በመከታተል ያስፈጽማል፤
የድርጅቱ ቢሮዎች ሕንፃ፣ ግቢና የመገልገያ መሣሪያዎች ወቅታዊ ጥገናና ዕድሳት እንዲደረግላቸው ይከታተላል፤
የእሳት አደጋ መከላከያዎች በየቦታው ተሟልተው እንዲቀመጡና በየአካባቢው ያሉ ሠራተኞችም በሙያው በቂ ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤
ለጥበቃ፣ ለጽዳት ሠራተኞች፣ ለተላላኪዎችና ለሰርቪስ ሾፌሮች ወዘተ…….አስፈላጊውን የሥራ ፕሮግራም በማውጣት ይደለድላል አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
የስልክ፣ የመብራትና የውሃ መስመሮች አገልግሎት ሲያቋርጡ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በአስቸኳይ በመነጋገር አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ያደርጋል፤
የፎቶ ኮፒና የህትመት አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ መስጠታቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
የስልክ አጠቃቀም፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ፍጆታ በቁጠባ እንዲሆን ይከታተላል፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን እየተከታተለ ያስፈጽማል፤
በአዲስ ወይም በነባር የሥራ መደቦች ላይ ሠራተኞች ለመመደብ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ በቅርብ ኃላፊው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለተወዳዳሪዎች ማስታወቂያ ያወጣል፣ ተወዳዳሪዎችንም ማስረጃዎቻቸውን አረጋግጦ ይመዘግባል፤
የሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት በወቅቱ ተሞልቶ በሠራተኞች የግል ማኅደር ውስጥ እንዲካተትና እንዲቀመጥ ያደርጋል፤
የሠራተኛ ቅጥር ወይም ዕድገትና ዝውውር እንዲሁም ጡረታና ስንብት በሚፈጸምበት ጊዜ አዋጅንና ኅብረት ስምምነቱን ተከትሎ አስፈላጊውን ይፈጽማል፤
የድርጅቱ የሥራ ሰዓትና የሥራ ዲሲፕሊን እንዲከበር ከሚመለከታቸው የሥራ ቅንጅት ይፈጥራል፣ የሠራተኞች የዲሲፕሊን ሁኔታ እንዲሻሻልና የሥራ ተነሳሽነት እንዲጎለብት አስፈላጊውን ሥልጠና ይሰጣል፤
የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ በማይጎዳ መንገድ ሠራተኞች የዓመት ዕረፍት ፈቃዳቸውን በወቅቱ እንዲወስዱ ከቅርብ ኃላፊው ጋር በመመካከር ፕሮግራም ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
የሠራተኞች ደመወዝና የትራንስፖርት አበል በወቅቱ እንዲከፈል ከሰዓት ቁጥጥር ሰራተኛ የሚቀርብለትን መረጃ መሠረት በማድረግ በማጣራትና በማረጋገጥ ዝርዝሩን በወቅቱ ለሂሳብ የሥራ ዘርፍ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤
የድርጅቱ ሠራተኞች የሚያቀርቡትን የሕክምና የተለያዩ የፈቃድ ማስረጃዎች ከአዋጁና ከድርጅቱ የአስተዳደር መመሪያ ጋር አመሳክሮና አረጋግጦ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ያስተላልፋል፤
በሠራተኞች የግል ማኅደሮች ውስጥ መያዝ የሚገባው መረጃዎችና ሰነዶች ተሟልተውና ሚስጥራቸው ተጠብቆ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤
በሥሩ ለሚገኙ ሠራተኞች ሚዛናዊ የሆነ የሥራ ሥምሪት ይሰጣል የሥራ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል ሪፖርት ያደርጋል፤
በተጨማሪም ሌሎ ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጠውን ተመሳሳይ ሥራዎችን ያከናውናል፤
ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ ኮሌጅ ዲግሪ ወይም በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ 12+4 ወይም በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ 10+3 በሥራ አመራር፣ ሕዝብ አስተዳደር ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች
3 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ላት
አመልካቾች የትምህርት፣ የሥራ ልምድ ደብዳቤ የማይመለስ ኮፒ ይዛችሁ በድርጅቱ ኢ-ሜይል: hrminaye@gmail.com ወይም ቃሊቲ ገብርኤል ኢንዱስተሪያል መንደር አካባቢ ዴሉክስ ፈርኒቸር ፋብሪካ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። ለበለጠ መረጃ ስልክ 0114717381
Fields Of Study
Public Administration
TVET
Management
Related Jobs
about 10 hours left
Gift Real Estate
Senior HR Officer
Human Resource Officer
Full Time
4 yrs
1 Position
Master's or Bachelor's Degree in Human Resource Management, Business Administration, or in a related field of study with relevant work experience Duties & Responsibilities: - Assist in the recruitment and onboarding of new employees, including posting job openings, conducting interviews, and preparing employment contracts. - Maintain and update employee records, ensuring accuracy and compliance with regulations. - Administer employee benefits programs and assist with payroll processing
about 10 hours left
Aforo Trading PLC
HR Manager
Human Resource Management Specialist
Full Time
5 yrs
1 Position
Bachelor's Degree in Human Resource Management, Public Administration, Management, or in a related field of study with relevant work experience Duties & Responsibilities: - Develop and implement HR policies, procedures, and strategies to support the company’s objectives. - Oversee the recruitment, selection, and onboarding process to ensure the company attracts and retains qualified professionals. - Design and manage employee performance appraisal systems, providing feedback and recommending development initiatives
1 day left
Santa Maria Construction PLC
Human Resources Administration & Department Head
Human Resource Management Specialist
Full Time
15 yrs
1 Position
Bachelor's Degree in Management, or in a related field of study, with relevant work experience, out of which 7 years on a specified position
1 day left
Tsruy Soap and Detergent Factory
Human Resource and General Service Head
Human Resource Officer
Full Time
4 - 6 yrs
1 Position
MA or BA Degree in Human Resource Management or in a related field of study with relevant work experience
1 day left
Dega Group Trading PLC
HR Officer
Human Resource Officer
Full Time
1 yrs
1 Position
Bachelor’s Degree in Management, or in a related field of study with relevant work experience Duties & Responsibilities: - Assist the end-to-end recruitment process like Job Posting, Screening and Interviews - Maintain proper communication between management and employee - Support the performance appraisal process and monitor employee performance metrics
2 days left
Mieyona Foam Private Limited Company
Factory HR Manager
Human Resource Management Specialist
Full Time
5 yrs
4 Positions
Bachelor’s Degree in Business Mgt & Leadership or in a related field of study with relevant work experience