Job Expired

company-logo

የፐርሶኔልና ጠቅላላ አገልግሎት

Minaye PLC

job-description-icon

Low and Medium Skilled Worker

Manufacturing Skilled Worker

------

2 years - 3 years

2 Positions

2024-04-30

to

2024-06-28

Required Skills
Required skills have not yet been specified for this position this job
Fields of study
No fields of study

Full Time

Share

Job Description

ዝርዝር የሥራ ተግባር 

  • የዋና ክፍሉን ሥራ ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ በሥሩ ያሉትን ሠራተኞች ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
  • በድርጅቱ የአስተዳደር ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት የድርጅቱን የሰው ሀይል ያስተዳድራል፣ ቀልጣፋ የአስተዳደር  ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤
  • በተለያዩ ምክንያት ድርጅቱን በሚለቁ ሠራተኞች ምትክ ተገቢው የሰው ኃይል እንዲተካ ለሚመለከታቸው የዘርፍ ሃላፊዎች ያሳውቃል፣ለቅጥሩም ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፤
  • ለድርጅቱ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የውኃ፣ የመብራት፣ የስልክ፣ የነዳጅ፣ የትራንሰፖርት፣ እንዲሁም ኢንሹራንስ፣ ለመዝናኛ ክበብ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች መሟላታቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ያልተሟሉ መገልገያዎችና ዕቃዎች ካሉ እንዲሟሉ ዝርዝር ሪፖርት ለቅርብ አለቃው ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
  • የጠቅላላ አገልግሎት ሥራ በተሻለ ቅልጥፍናና ጥራት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ጥናት በማድረግ ለሃላፊው አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፤ ለክፍሉ የሚያስፈልገውን በጀት በማዘጋጀት ያስፈቅዳል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል ያረጋግጣል፤
  • የድርጅቱ የግቢ ጥበቃ አስተማማኝ መሆኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
  • ለድርጅቱ ሠራተኞች የሚያስፈልጉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ መሣሪያዎችና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች በወቅቱ መሟላታቸውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፤
  • በድርጅቱ ደንብና መመሪያ መሠረት ለሠራተኞች መስጠት የሚገባው የሥራ ላይ የአደጋ መከላከያ የሥራ ልብስና የመሳሰሉት በወቅቱ እንዲደርሳቸው ያደርጋል፡፡
  • በኢንሹራንስ ፖሊሲ መሠረት የድርጅቱ ንብረትና የድርጅቱ ሠራተኞች የመድን ዋስትና ማግኘታቸውን ይከታተላል፤ በየዘመኑ መታደሱን ያረጋግጣል፤
  • በንብረት ወይም በሰው ላይ አደጋ በደረሰ ጊዜ በተገቢው የመድን ዋስትና መሠረት የካሳ ጥያቄ /claim/ በማድረግ ተከታትሎ ያስፈጽማል፤
  • የተሽከርካሪዎች የሕይወት ታሪክ፣ የነዳጅና የቅባት ፍጆታ የጥገና ወጪን በተመለከተ አስፈላጊ መረጃዎች በሙሉ መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
  • ማንኛውም የድርጅቱ ንብረት ተገቢ ጥበቃና ጽዳት የተሟላ መሆኑን፣ የቢሮ መሣሪያዎች፣ ቋሚ ንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎችና ሕንፃዎች አስፈላጊው ጥገናና ዕድሳት በሚያስፈልጋቸውና ከቅርብ አለቃው ሲፈቀድ በሚተላለፍለት መመሪያ መሠረት ጥገናዎቹ በወቅቱ እንዲከናወኑ በመከታተል ያስፈጽማል፤
  • የድርጅቱ ቢሮዎች ሕንፃ፣ ግቢና የመገልገያ መሣሪያዎች ወቅታዊ ጥገናና ዕድሳት እንዲደረግላቸው ይከታተላል፤
  • የእሳት አደጋ መከላከያዎች በየቦታው ተሟልተው እንዲቀመጡና በየአካባቢው ያሉ ሠራተኞችም በሙያው በቂ ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤
  • ለጥበቃ፣ ለጽዳት ሠራተኞች፣ ለተላላኪዎችና ለሰርቪስ ሾፌሮች ወዘተ…….አስፈላጊውን የሥራ ፕሮግራም በማውጣት ይደለድላል አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
  • የስልክ፣ የመብራትና የውሃ መስመሮች አገልግሎት ሲያቋርጡ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በአስቸኳይ በመነጋገር አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ያደርጋል፤
  • የፎቶ ኮፒና የህትመት አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ መስጠታቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
  • የስልክ አጠቃቀም፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎት ፍጆታ በቁጠባ እንዲሆን ይከታተላል፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን እየተከታተለ ያስፈጽማል፤
  • በአዲስ ወይም በነባር የሥራ መደቦች ላይ ሠራተኞች ለመመደብ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ በቅርብ ኃላፊው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለተወዳዳሪዎች ማስታወቂያ ያወጣል፣ ተወዳዳሪዎችንም ማስረጃዎቻቸውን አረጋግጦ ይመዘግባል፤
  • የሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት በወቅቱ ተሞልቶ በሠራተኞች የግል ማኅደር ውስጥ እንዲካተትና እንዲቀመጥ ያደርጋል፤
  • የሠራተኛ ቅጥር ወይም ዕድገትና ዝውውር እንዲሁም ጡረታና ስንብት በሚፈጸምበት ጊዜ አዋጅንና ኅብረት ስምምነቱን ተከትሎ አስፈላጊውን ይፈጽማል፤
  • የድርጅቱ የሥራ ሰዓትና የሥራ ዲሲፕሊን እንዲከበር ከሚመለከታቸው የሥራ ቅንጅት ይፈጥራል፣ የሠራተኞች የዲሲፕሊን ሁኔታ እንዲሻሻልና የሥራ ተነሳሽነት እንዲጎለብት አስፈላጊውን ሥልጠና ይሰጣል፤
  • የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ በማይጎዳ መንገድ ሠራተኞች የዓመት ዕረፍት ፈቃዳቸውን በወቅቱ እንዲወስዱ ከቅርብ ኃላፊው ጋር በመመካከር ፕሮግራም ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የሠራተኞች ደመወዝና የትራንስፖርት አበል በወቅቱ እንዲከፈል ከሰዓት ቁጥጥር ሰራተኛ የሚቀርብለትን መረጃ መሠረት በማድረግ በማጣራትና በማረጋገጥ ዝርዝሩን በወቅቱ ለሂሳብ የሥራ ዘርፍ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤
  • የድርጅቱ ሠራተኞች የሚያቀርቡትን የሕክምና የተለያዩ የፈቃድ ማስረጃዎች ከአዋጁና ከድርጅቱ የአስተዳደር መመሪያ ጋር አመሳክሮና አረጋግጦ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ያስተላልፋል፤
  • በሠራተኞች የግል ማኅደሮች ውስጥ መያዝ የሚገባው መረጃዎችና ሰነዶች ተሟልተውና ሚስጥራቸው ተጠብቆ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤
  • በሥሩ ለሚገኙ ሠራተኞች ሚዛናዊ የሆነ የሥራ ሥምሪት ይሰጣል የሥራ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል ሪፖርት ያደርጋል፤
  • በተጨማሪም ሌሎ ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጠውን ተመሳሳይ ሥራዎችን ያከናውናል፤

የማመልከቻ መመርያ

  • አመልካቾች የትምህርት፣ የሥራ ልምድ ደብዳቤ የማይመለስ ኮፒ ይዛችሁ በድርጅቱ ኢ-ሜይል hrminaye@gmail.com ወይም ቃሊቲ ገብርኤል ኢንዱስተሪያል መንደር አካባቢ ዴሉክስ ፈርኒቸር ፋብሪካ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። ለበለጠ መረጃ ስልክ 0114717381

Related Jobs

2 days left

Amaco General Trading

Product Quality Controller

Quality Control Supervisor

time-icon

Full Time

2 yrs

4 Positions


Educational Background in a related field of study with relevant work experience

Addis Ababa

13 days left

Aniska food Factory

Oven operator

Machine Operator

time-icon

Full Time

2 yrs

1 Position


TVET Level I in Industrial Electricity, Mechanics, or in a related field of study with relevant work experience

Addis Ababa

13 days left

Aniska food Factory

Sugar Grinder Machine Operator

Machine Operator

time-icon

Full Time

1 yrs

1 Position


Completion of 10th Grade with relevant work experience

Addis Ababa

13 days left

Aniska food Factory

A/Mixer operator

Machine Operator

time-icon

Full Time

0 yrs

1 Position


TVET Level 10+1 in Industrial Electricity, Mechanics, or in a related field of study Duties & Responsibilities: - Operate mixing and blending machines - Read and interpret mixing instructions and recipes - Measure and load ingredients into mixer machines

Addis Ababa

13 days left

Aniska food Factory

Cooling and Stacker Operator

Machinery Operator

time-icon

Full Time

0 yrs

1 Position


Completion of 10th Grade Duties & Responsibilities: - Operate various mechanical and electronic test equipment

Addis Ababa

13 days left

Aniska food Factory

A/Sugar Grinder Machine Operator

Machinery Operator

time-icon

Full Time

1 yrs

1 Position


Completion of 10th Grade with relevant work experience

Addis Ababa